የደብረ ገነት መድኃኔዓለም የመረዳጃ ማኅበር አጭር ታሪክ፤ ﷯ይህ የእድር መረዳጃ ማኅበር ሊመሠረት የቻለው፤ ይኸውም በ1997 (1989 E.C.) ሃሳቡን በቅድሚያ ያቀረቡት ሶስት የቤተ ክርስቲያን አዛውንት (ሀ)ሻለቃ ኃይለማርያም አባይ (ለ)አቶ ንጋቱ ጥላሁንና (ሐ)ኢንጂኔር ግርማ አላሮ ሲሆኑ፤ ማሕበሩ ግን በአባላት ፀድቆ በሕግ የተቋቋመው በ2004 (1996 E.C.) ነው። የተመሠረተው ማኅበር በ“IRS Code 501 (C) (3)” የትርፍ አልባ ድርጅት ሕግ ተመርኩዞ ነው። የሞት አደጋ ወይንም ሕመም ሲያጋጥም እርስ በእርስ ለመረዳዳትና ለመፅናናት የተቋቋመ በመሆኑም፣ በሐገር ውስጥ ገቢ የአስተዳደር ደንብ መሠረትም ድርጅቶችና ግለሰቦች ለማሕበሩ የሚያደርጉት አስተዋፅፆ ከቀረጥ ነፃ ነው። የድርጅቱ ዋና ዓላማ፤ የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም የመረዳጃ ማኅበር ቤተሰቦችን በሀዘንና በሕመም ጊዜ እርስ በርስ ለማፅናናትና ለመረዳዳት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በማመንና፣ እንዲሁም ባለው የኑሮ ጠባይ ምክንያት ለመቀራረብ ባለመቻሉ፣ ግንኙነትን ለመፍጠር ይህ ድርጅት ተቋቁሟል። አንድ የቤተ ክርስቲያን አባል፤ በተጨማሪ የእድሩም አባል መሆን ከወሰነ በመተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የተዘረዘሩትን የአባልነት መስፈርቶች በቅድሚያ ማሟላት ይገባዋል። አባልነት ጊዜ የሚጀምረውም ከተመዘገበበት ዕለት ጀምሮ ይሆናል። ማሕበሩ የሚተዳደረው (ሀ)ከአባላት ወርሃዊ መዋጮ፤ (ለ)ከደንብ ማስከበሪያ ከሚገኝ ገቢና (ሐ) ከሌሎች ልዩ ልዩ የገንዘብ አመንጪ ከሚሰበሰብ የባጀት ገቢ ነው ። የአባልነት ግዴታ፤ ➢ ማሕበርተኛ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ በፀሎተ ፍትሐት ላይ መገኘት፤ ➢ በቀብር ሥነ ስርዓት ላይ መድረስና ቤተሰቡን ማጽናናት፤ ➢ በሕመምና በሀዘን ሰዓት በመገኘት የተጠናከረ ማሕበራዊ ግንኙነትን መፍጠር፤ በጥቅምት 2015 (2008 E.C) በሶስት አድራሻዎች በቨርጂንያ እና በሜሪላንድ አካባቢ የመቃብር ቦታዎች (Plots) እንዲገዙ ተወስኗል። የተመረጡት የመቃብር ክልል ቦታዎች፣ ለደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለአባላት መኖርያ ሰፈር የሚቀርቡ አማካኝ ቦታዎች ላይ ነው። • Fairfax Memorial Park Cemetery in Virginia • Resurrection Cemetery in Maryland • Gate of Heaven Cemetery in Maryland

DGMAMAA Mutual Aid Association (IDIR) History

 

Debre Genet MedhaneAlem Mutual Aid Association (IDIR) was first introduced in 1997 (1989 E.C.), and

formally established in 2004 (1996 E.C.) by a small group of MedhaneAlem Church Members.

The primary objective of the Association is to support association members and their families financially

and spiritually in times of bereavement and serious illness.

 

The Association was established as a tax-exempt nonprofit organization in accordance with

Internal Revenue Code 501 (C) (3) and has no affiliations with any political organization.

 

In order to join the DGMAMMA (IDIR) an applicant must be a member of the Debre Genet MedhaneAlem

Church for one year. After one year, the member is granted the full benefits of the association’s membership.

 

DGMAMAA was launched to enable the association’s members to collectively leverage their financial and human resources to provide support and funds to ameliorate the difficulties members confront in times of serious illnesses and death.

 

DGMAMAA is long-term group life coverage with minimal and affordable monthly contributions.

The monthly membership contributions are collected and distributed as specified in the Association’s bylaws to assist the grieving IDIR member and their families.

 

Members are required to:

➢ Attend Church Memorial Services

➢ Attend Funerals/Burial Services

➢ Comfort grieving family members (Attend LEKSO)

 

In 2015 (2007 E.C.) the Association purchased several burial lots in three different Cemeteries:

• Fairfax Memorial Park Cemetery in Virginia

• Resurrection Cemetery in Maryland

• Gate of Heaven Cemetery in Maryland

 

DGMAMAA will assist its members with funeral expenses following the loss of a family member.

 

 

 

ደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም መረዳጃ ማሕበር፤ Date = 2003-4 / 1996-8 After electing Major Hailemariam Abai to preside over the meeting, The Following Members are involved in the creation of the Association በሻለቃ ኃይለ ማርያም አባይ ዋና ሰብሳቢነት ማሕበሩን ያዋቀሩት አባላት፤ • ሻለቃ ኃይለ ማርያም አባይ - (ዋና ሰብሳቢ)፤ • ሊቀ ዲያቆን ጌታሁን አጥላው ------(አባል)፤ • አቶ ንጋቱ ጥላሁን -----------------(አባል)፤ • አቶ ዘለቀ በለጠ --------------------(አባል)፤ • ወሮ ተቋመች ታደሠ ---------------(አባል)፤ • ሻምበል ታደሠ ጥላሁን ------------(አባል)፤ • አቶ ተመስገን ጎበና --------------- (አባል)፤ • አቶ ደምሰው ተስፋዬ --------------(አባል)፤ • አቶ ሠይፉ ከርሴ ------------------(አባል)፤ • አቶ ይግዛው መንበሩ --------------(አባል)፤ • አቶ ግርማ አላሮ ------------------(አባል)፤ • ወሮ ደስታ በየነ -------------------(አባል)፤